Call experts

+251 9750 705 03

Call for the 9th ordinary and 5th extraordinary general shareholders meeting.

የባለ አክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔ ጥሪ

ለተከበራችሁ የሸገር የሸገር ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ፥

በኢትዮጵያ ንግድ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 አንቀጽ 366 (1)፣367 (1) እና አንቀጽ 370 እንዲሁም በተሻሻለዉ የአክሲዮን ማህበሩ የመመስረቻ ጽሁፍ አንቀጽ 13 መሠረት የሸገር ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ ባለአክስዮኖች 9ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔና 5ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ  ሕዳር 19 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በአዲስ አበባ ቂርቆስ ክ/ከተማ በኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል አዳራሽ ስለሚካሄድ ባለአክሲዮኖች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተጠቀሰው ቀን፣ሰዓትና ቦታ በጠቅላላ ጉባዔዉ ላይ እንዲገኙ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያቀርባል፡፡ 

  1. አክሲዮን ማህበሩን የሚመለከቱ  ዋና ዋና መረጃዎች
  2. የአክሲዮን ማህበሩ ስም፡-          ሸገር ማይክሮ ፋይናንስ አክሲዮን ማህበር
  3. የአክሲዮን ማህበሩ አይነት፡-       በአነስተኛ የፋይናንስ ሥራ ላይ የተሰማራ
  4. የማህበሩ የተፈረመ ካፒታል፡       77,223,000 /ሰባ ሰባት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሀያ ሶስት ሺህ ብር
  5. የማህበሩ የተከፈለ ካፒታል፡-      77,223,000 /ሰባ ሰባት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሀያ ሶስት ሺህ ብር
  6. የማህበሩ የንግድ ምዝገባ ቁጥር፡-  NL/AA/3/00112632/200
  7. የአክሲዮን ማህበሩ ድረገጽ፡        www.shegermicrofinance.com
  8. የማህበሩ ዋና መስሪያ ቤት፡-     አዲስ አበባ፣ን/ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 02፣ኤስ ሳራ ታዎር 6ኛ ፎቅ
  • የባለአክሲዮኖች 9ኛ (ዘጠነኛ) መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች
  • አዳዲስና ነባር ባለአክሲዮኖችን መቀበልና ማጽደቅ (ከህዳር 16/2018 ዓ.ም በፊት የተሸጡና በጠቅላላ ጉባዔ ያልጸደቁ)
  • እ.ኤ.አ የ2025/2026 በጀት ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥና በቀረበዉ ሪፖርት ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፤
  • እ.ኤ.አ የ2025/2026 በጀት ዓመት የውጭ ኦዲተር ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥና በቀረበዉ ሪፖርት ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፤
  • እ.ኤ.አ 2025/2026 በጀት ዓመት ትርፍና ኪሳራ አደላደልና አከፋፈል ላይ የቀረበዉን የዉሳኔ ሀሳብ ተወያይቶ ማፅደቅ
  • እ.ኤ.አ 2026/2027 በጀት ዓመት ለዳይረክተሮች ቦርድ አባላት ስለሚከፈል ዓመታዊ የድካም ዋጋ መወሰን
  • ዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት መምረጥ
  • እ.ኤ.አ ከ2026/2027 እስከ 2028/2029 በጀት ዓመት ድረስ የሚያገለግሉ የዉጭ ኦዲተርን መሾምና ክፍያቸዉን ማጽደቅ፤
  • የመደበኛ ጠቅላላ ጉባዔዉን ቃለ ጉባዔ ማጽደቅ
  • የባለአክሲዮኖች 5ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች
  • የሸገር ማይክሮ ፋይናንስ አክሲዮን ማህበር መመስረቻ ጽሁፍ አንቀጾችን መሻሻልና አዳዲስ አንቀጾችን መጨመር
  • የተቋሙ የተከፈለ ካፒታል ማሳደግ ላይ ተወያይቶ ዉሳኔ ማስተላለፍ
  • የመደበኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔዉን ቃለ ጉባዔ ማጽደቅ
  • ማሳሰቢያ፡-
  • በጉባዔዉ ላይ በአካል መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮን ከስብሰባው ዕለት ሦስት ቀናት በፊት በማህበሩ ዋና መስሪያ ቤት መካኒሳ ኤስ ሳራ ህንፃ 6ኛ ፎቅ በመገኘት አክሲዮን ማህበሩ ባዘጋጀው የውክልና መስጫ ቅጽ ላይ በመሙላት ተወካዮቻቸሁን ማሳተፍ ይችላሉ ፡፡
  • እንዲሁም ተወካዮቻቸሁ አግባብ ካለዉ የፌደራል ወይም የክልል የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት የተሰጠዉ በስብሰባ ለመሳተፍና ድምፅ ለመስጠት የሚያስችል የዉክልና ሰነድ ዋናዉንና ፎቶ ኮፒዉን ይዘዉ በመቅረብ መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡
  • ባለአክሲዮኖች ወይም ወኪሎች ወደ ስብሰባ ቦታ ስትመጡ ማንነታቸሁን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ፤ፓስፖርት፣ብሔራዊ መታወቂያ ወይም መንጃ ፍቃድ ይዛችሁ መቅረብ ይኖርባችዋል፡፡
  • ተወካዮች የወካያቸዉን ኢትዮጵያዊ ወይም ትዉልድ ኢትዮጵያዊ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የታደሰ መታወቂያ ፤ብሔራዊ መታወቂያ፤ ፓስፖርት ወይም መንጃ ፍቃድ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡

የዳይሬክተሮች ቦርድ

ሸገር ማይክሮፋይናንስ  አ.ማ

Add a Comment

Your email address will not be published.