Call experts

+251 9750 705 03

Call for the 8th ordinary general shareholders Meeting.

የጠቅላላ ጉባዔ ስብሰባ ጥሪ
ለተከበራችሁ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

በኢትዮጵያ ንግድ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 አንቀጽ 366 (1)፣ 367 (1) እና አንቀጽ 370 እንዲሁም የአክሲዮን ማህበሩ የተሻሻለዉ የመመስረቻ ጽሁፍ አንቀጽ 13 መሠረት የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክስዮኖች 8ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔና 4ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ህዳር 27/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በአዲስ አበባ ቂርቆስ ከ/ከተማ በኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል አዳራሽ ስለሚካሄድ ባለአክሲዮኖች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተጠቀሰው ቀን፣ሰዓትና ቦታ በጠቅላላ ጉባዔዉ ላይ እንዲገኙ የማህበሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

1.ማህበሩን የሚመለከቱ ዋና ዋና መረጃዎች
የአክሲዮን ማህበሩ ስም፡- ሸገር አነስተኛ የፋይናንስ አክሲዮን ማህበር
የአክሲዮን ማህበሩ አይነት፡- በአነስተኛ የፋይናንስ ሥራ ላይ የተሰማራ
የአክሲዮን ማህበሩ የተፈረመ ካፒታል፡ 76,600,000 /ሰባ ስድስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ብር
የአክሲዮን ማህበሩ የተከፈለ ካፒታል፡- 76,600,000 /ሰባ ስድስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ብር
የማህበሩ የንግድ ምዝገባ ቁጥር፡- NL/AA/3/00112632/200
የማህበሩ ዋና መስሪያ ቤት፡- አዲስ አበባ ከተማ፣ን/ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 02፣የቤት ቁጥር አዲስ፣ኤስ ሳራ ታዎር 6ኛ ፎቅ
የአክሲዮን ማህበሩ ድረገጽ፡https፡//shegermfisc@gmail.com

2.የባለአክሲዮኖች 8ኛ (ስምንተኛ) መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች
1.የተተኪ ዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ሹመት ማጽደቅ ወይም አዳዲስ አባላትን መምረጥ
2.አዳዲስና ነባር ባለአክሲዮኖችን መቀበልና ማጽደቅ
3.አ.ኤ.አ የ2024/2025 በጀት ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥና በቀረበዉ ሪፖርት ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ
4.አ.ኤ.አ የ2024/2025 በጀት ዓመት የውጭ ኦድተር ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥና በቀረበዉ ሪፖርት ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ
5.አ.ኤ.አ ከ2025/2026 እስከ 2027/2028 በጀት ዓመት ድረስ የሚያገለግሉ የዉጭ ኦድተርን መሾምና ክፍያቸዉን ማጽደቅ
6.አ.ኤ.አ 2024/2025 በጀት ዓመት ትርፍና ኪሳራ አደላደልና አከፋፈል ላይ የቀረበዉን የዉሳኔ ሀሳብ ተወያይቶ ማፅደቅ
7.አ.ኤ.አ 2025/2026 በጀት ዓመት ለዳይረክተሮች ቦርድ አባላት ስለሚከፈል ዓመታዊ የድካም ዋጋ መወሰን
8.የመደበኛ ጠቅላላ ጉባዔዉን ቃለ ጉባዔ ማጽደቅ

3.የባለአክሲዮኖች 4ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች
1.የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ አክሲዮን ማህበር የስም ለውጥና የሎጎ ለውጥ እንዲሁም አዲስ በቀረበዉ ከወለድ ነፃ የፋይናንስ አገልግሎት ስምና ሎጎ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ መስጠት
2.ተቋሙ በኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ መመዝገብ እና አክሲዮኖችን ለህዝብ ለማቅረብ የሚችልበትን አግባብ በተመለከተ በቀረቡት የዉሳኔ ሀሳብ ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ
3.በወረቀት ያሉ አክሲኖችን በሙሉ ወደ ግዑዝ አልባ ወይም ኤሌክትሮኒክስ አክሲዮን እንዲተኩ በቀረበዉ የዉሳኔ ሀሳብ ላይ ተወያይቶ መወሰን
4.የመደበኛ አስቸኳይ ጉባዔዉን ቃለ ጉባዔ ማጽደቅ

4.ማሳሰቢያ፡-
በጉባዔዉ ላይ በአካል መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮን ከስብሰባው ዕለት ሦስት ቀናት በፊት በመህበሩ ዋና መስሪያ ቤት መካኒሳ ኤስ ሳራ ህንፃ 6ኛ ፎቅ በመገኘት አክሲዮን ማህበሩ ባዘጋጀው የውክልና መስጫ ቅጽ ላይ በመሙላት ተወካዮቻቸሁን ማሳተፍ ይችላሉ፡፡
እንዲሁም ተወካዮቻቸሁ አግባብ ካለዉ የፌደራል ወይም የክልል የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት የተሰጠዉ በስብሰባ ለመሳተፍና ድምፅ ለመስጠት የሚያስችል የዉክልና ሰነድ ዋናዉንና ፎቶ ኮፒዉን ይዘዉ በመቅረብ መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡
ባለአክሲዮኖች ወይም ወኪሎች ወደ ስብሰባ ቦታ ስትመጡ ማንነታቸሁን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ፤ፓስፖርት፣ብሔራዊ መታወቂያ ወይም መንጃ ፍቃድ ይዛችሁ እንድታቀርቡ፡፡
እንዲሁም ተወካዮች የወካያቸዉን ኢትዮጵያዊ ወይም ትዉልድ ኢትዮጵያዊ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የታደሰ መታወቂያ ፤ብሔራዊ መታወቂያ፤ ፓስፖርት ወይም መንጃ ፍቃድ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡

ሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ
የዳይሬክተሮች ቦርድ

ለበለጠ መረጃ፣
09 27 11 11 14
09 75 07 22 03

Add a Comment

Your email address will not be published.